Skip to main content

This is archived content from the U.S. Department of Justice website. The information here may be outdated and links may no longer function. Please contact webmaster@usdoj.gov if you have any questions about the archive site.

Press Release

የፍትህ ዲፓርትመንት እና የኮሎራዶ የህግ ተርጓሚ በፍርድ ቤት ውስጥ ውስን የሆነ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች የቋንቋ ተደራሽነት አሻሽለዋል።

For Immediate Release
Office of Public Affairs

የኮሎራዶ የህግ ተርጓሚ አካላት ውስን የሆነ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው ሰዎች (LEP) እና የፍርድ ቤት ጉዳይ ያላቸው ሰዎች ትርጉም ያለው የቋንቋ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ትልቅ እርምጃ መውሰዳቸውን የህግ ክፍል በዛሬው እለት አሳውቋል።

ጁላይ 2023 ላይ የዲፓርትመንቱ የሲቪል መብቶች ክፍል የኮሎራዶ ህግ ተርጓሚን ያገኘ ሲሆን ይህም የሆነው ፍርድ ቤቶች ውስን የሆነ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ላላቸው ሰዎች በሲቪል መብቶች አዋጅ 1964 (ርእስ VI) መሰረት አስፈላጊ የሆነ የቋንቋ አገልግሎት ካለማቅረባቸው ጋር በተያያዘ ቅሬታ ከተቀበለ በኋላ ነው። ርእስ VI በዘር፣ ቀለም እና የፌደራል ፋይናንስ ድጋፍን ለሚቀበሉ በብሄራዊ መገኛ መሰረት ማግለልን ይከለክላል።

ክፍሉ ባቀረበው የምርመራ ጥያቄ መሰረት የኮሎራዶ የህግ ተርጓሚ የተነሱትን ቅሬታዎች በሚመለከት ቀድመው የተወሰዱ እርምጃዎችን የለየ ሲሆን ከቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ጋር በተያያዘ ተጨማሪ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ከክፍሉ ጋር ስራ ሰርቷል።

“ትክክለኛ እና ጊዜውን የጠበቀ የማስተርጎም አገልግሎት በፍርድ ቤት ውስጥ ማቅረብ ሁሉም የፍርድ ቤት ተጠቃሚዎች እኩል የሆነ የፍትህ ተደራሽነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ቁልፍ ነገር ነው” ሲሉ የፍትህ ክፍሉ የሲቪል መብቶች ምክትል አቃቤ ህግ ክሪስቲን ክላርክ ተናግረዋል። “በኮሎራዶ የህግ ተርጓሚ የተወሰዱት እርምጃዎች ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ ሲሆን ጠንካራ የሆነ የቋንቋ ተደራሽነትን ለማቅረብ ያለውን እውነተኛ ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ነው።"

DOJ ከኮሎራዶ የህግ ተርጓሚ ጋር መስራት ከጀመረበት አመት ጀምሮ ፍርድ ቤቱ አዲስ የቋንቋ ተደራሽነት አስተባባሪን ቀጥሯል፣ የቋንቋ ተደራሽነት ፋይናንስ ፖሊሲን ከልሷል፣ አዲስ የቀጠሮ ስርአትን ለአስተርጓሚዎች ዘርግቷል፣ የጆሮ ማዳመጫ እና አይፓዶችን ጨምሮ ለፍርድ ቤት ማስተርጎም አገልግሎት እንዲሆን አዳዲስ መሳሪያዎችን ገዝቷል፣ የፍርድ ቤት ሰራተኞችን እና አስተርጓሚዎችን አሰልጥኗል እና ሌሎች ቁልፍ የሆኑ ማሻሻያዎችን ተግብሯል።

ክፍሉ የእነዚህን ለውጦች መተግበር መቆጣጠር ይቀጥላል እና ከህዝቡ ደግሞ ግብረመልሶችን ይቀበላል። ከማግለል ጋር ግንኙነት ያላቸው ቅሬታዎች በሲቪል መብቶች ክፍል ድረገጽ civilrights.justice.gov በኩል መቅረብ ይችላሉ።

ስለ ሲቪል መብቶች ክፍል ተጨማሪ መረጃ በ www.justice.gov/crtይገኛል። ውስን የሆነ የቋንቋ ችሎታ መረጃ እና ርእስ VI www.lep.gov ላይ የሚገኝ ሲሆን ከፍርድ ቤቶች ጋር ግንኙነት ያለው መረጃ ደግሞ www.lep.gov/state-courts ላይ ይገኛል። 

Updated February 6, 2025

Civil Rights
Press Release Number: 24-1248