Skip to main content
Press Release

የፍትህ ሚኒስቴር፤ ለሕግ ማስከበሪያ እርምጃ የሚውል አዲስ የቋንቋ ተደራሽነት ማስጀመሩን አስታወቀ

በተጨማሪም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዴንቨር የፖሊስ መምሪያን የቋንቋ ተደራሽነት አስመልክቶ ላካሄደው ምርመራ የደረሰበትን የመፍትሄ ሃሳብ አስታውቋል

የፍትህ ሚንስቴር በሃገር አቀፍ ደረጃ የህግ አስከባሪ አካላት፤ ውሱን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ላላቸው የማህበረሰብ አባላት ትርጉም ባለው እና ተገቢ በሆነ የቋንቋ ድጋፍ በመታገዝ ግዴታቸውን እንዲወጡ ለመርዳት ለህግ ማስከበር አገልግሎት የሚጠቅም የቋንቋ ተደራሽነት እርምጃ ማስጀመሩን አስታውቋል።
የዚህ ሃሳብ ተነሳሽነት የሚኒስቴር መስርያ ቤቱ የህግ አስከባሪ አካላት በቋንቋ ተደራሽነት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ እየተወጡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለረዥም ግዜ ሲያደርግ የነበረው ጥረት ላይ የሚገነባ ይሆናል።   

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዜጎች መብቶች ክፍል ረዳት አቃቤ ህግ የሆኑት ክሪስተን ክላርክ ሲናገሩ፣
“የህግ አስከባሪ አካላት ውጤታማ እና ትርጉም ያለው የቋንቋ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ የሚያስፈልጋቸውን መሳርያ መስጠት፤ ውሱን የሆነ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ከህግ አስከባሪ አባላት ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት አስተማማኝነት የሚያራምድና የሚያሳድግ ይሆናል።” “የፍትህ ሚኒስቴር በዚህ የሃሳብ አነሳሽነት የተካተቱ የቋንቋ ተደራሽነት ምርጥ ተሞክሮዎችን እና መሰል ግብአቶችን በመላው ሃገሪቱ የሚገኙ የህግ አስከባሪ አካላት እንዲጋሩ ለማድረግ  ያስችለዋል” በማለት ክሪስተን ክላርክ ጨምረው ገልጸዋል።  

ይህ እርምጃ በዜጎች መብቶች መምሪያ የፌዴራል ማስተባበርያና የክትትል ማስከበሪያ ክፍል ከዩናይትድ ስቴትስ የአቃቤ ህግ ጽህፈት ቤቶች ጋር በመተባበር የሚመራ ይሆናል። በተለይም ይህ እርምጃ:

  • የአካባቢ እና የግዛት የህግ አስከባሪ አካላት በክልላቸው ከሚኖሩ ውሱን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆኑ       ግለሰቦችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ትርጉም ያለው የቋንቋ ተደራሽነት አገልግሎት             ለማቅረብ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ የቴክኒክ ድጋፍ እና ሌሎች ግብአቶችን ያጎለብታል።
  • የቋንቋ ተደራሽነት መመሪያዎቻቸውን፣ እቅዶቻቸውን፣ እና ስልጠናቸውን ለመገምገም ፣ ለማዘመን ወይም ለማጠናከር የሚፈልጉ የህግ አስከባሪ አካላትን በአዎንታዊ መልክ ያሳትፋል።
  • የቋንቋ ተደራሽነት ግንዛቤን ለመጨመር እና የህግ አስከባሪ አካላትን መልካም ተሞክሮ እና ግዴታ በሰፊው ለማበረታታት፣ ከዩናይትድ ስቴትስ የአቃቤ ህግ ጽህፈት ቤቶች ጋር በመተባበር ስልጠናዎችን      ያከናውናል።
  • የሚኒስቴሩ መስርያ ቤት ውሱን የእንግሊዝኛ የመግባባት ችሎታ ካላቸው የማህበረሰብ አባላት ጋር   የሚኖረውን መልካም ግንኙነትና ስምሪት ያጠናክራል።

ከዛሬው የእርምጃ ሃሳብ ማስታወቅያ በተጨማሪ የፍትህ ሚኒስቴር እና የዩናይትድ ስቴትስ የኮሎራዶ ግዛት የአቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት  የዴንቨር የፖሊስ መምርያ ውሱን የእንግሊዝኛ ችሎታ ባላቸው የህብረተሰብ አባላት ላይ በ1964 ዓም  የተደነገገውን የዜጎች  መብቶች ሕግ አንቀጽ VI  በጣሰ ሁኔታ ብሔራዊ ማንነትን መሰረት ያደረገ አድልዎ ይፈጽማል ተብሎ በቀረበበት ውንጀላ ተጀምሮ የነበረውን  ምርመራ በስምምነት ለማጠናቀቅ  መግባባታቸውን አስታውቀዋል።

የዚህ ሕግ አንቀጽ VI ፤ የፌዴራል የገንዘብ እገዛ  የሚደረግላቸው አካላት ዘርን ፣የቆዳ ቀለምን፣ ወይም ብሄራዊ ማንነትን መሰረት ያደረገ አድልዎን እንዳያደርጉ ይከለክላል።   

“ይህ ከዴንቨር የፖሊስ መምሪያ ጋር የተደረሰው ስምምነት የፖሊስ አባላት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ይረዳቸዋል፤” ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ ህግ ኮድ 28 § 515 አማካይነት በተሰጠ ስልጣን መሰረት ለኮሎራዶ ግዛት የዩናይትድ ስቴትስ ጠበቃ የሆኑት ማቲው ከርሽ ገልጸዋል።” “ማህበረሰብን የመድረስ ተግባር ሲያከናውኑም ሆነ ሕግ የጣሱ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚያደርጉት ጥረት ትክክለኛ የሆነ የቋንቋ አገልግሎት ማረጋገጥ፤የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ላይ በማያተኩር መልኩ፤ የፖሊስ መኮንኖች ሁሉንም የማህበረሰብ አባላት ለማገልገልና ጥበቃም ለማድረግ ያስችላቸዋል፣ በማለት ማቲው ከርሽ ጨምረው ገልጸዋል። 

የፍትህ ሚኒስቴር በዴንቨር የፖሊስ መምሪያ ላይ ይህንን ምርመራ የጀመረው በዴንቨር ምስራቃዊ ኮልፋክስ አካባቢ የሚኖሩ እና ዝቅተኛ የሆነ የእንግሊዘኛ ችሎታ ያላቸው የበርማ እና የሮሂንግያ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ነዋሪዎች በፖሊስ መምርያው ላይ ባቀረቡት ቅሬታ የተነሳ ነው።
ምርመራው፤ የዴንቨር ፖሊስ መምሪያ አባላት፤ ዝቅተኛ የእንግሊዝኛ ችሎታ ላላቸው አባላት የቋንቋ እገዛ እንደማያቀርቡ፣ ቢያቀርቡም ተገቢ እና ብቃት ያለው እንዳልሆነ በዛ ባሉ አጋጣሚዎች አሳይቷል።  ለምሳሌ፣ ይህ ምርመራ አስተማማኝና ተጨባጭ የሆነ የቋንቋ እገዛ የሚያስፈልግበትን ሁኔታዎች  ጨምሮ፣ የፖሊስ መምርያው አባላት፣ ልጆችን፣የቤተሰብ አባላትን፣ ወይም ተመልካቾችን የቋንቋ ድጋፍ እንዲያደርጉ አመኔታ ጥለውባችው እንዳነበረ በተደጋጋሚ አሳይቷል።   

በዚህ የመግባቢያ ስምምነት መሰረት፣ የዴንቨር ፖሊስ መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ፤ በቋንቋ ተደራሽነት መመሪያዎች፣ የአሰራር ስርአቶችና ስልጠናን የተመለከቱ ተከታታይ ለውጦችን ተግባራዊ ለማድረግ ተስማምቷል: 

  • ምስክሮችንና ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ፤ ዝቅተኛ የእንግሊዝኛ መግባባት ችሎታ ካላቸው ግለሰቦች ጋር ለመግባባት የሚያግዛቸውን አሰራር ለመዘርጋት የቋንቋ ተደራሽነት መመሪያና እና እቅዳቸውን ለማዘመን፤ እንዲሁም፤ አጣዳፊ ከሆኑ ሁኔታዎች በስተቀር፤ ህጻናትን፤ የቤተሰብ አባላትና ተመልካቾችን መጠቀምን ለማስወገድ፤
  • በሁሉም የዴንቨር ፖሊሰ ጣብያ ዞኖች ለመጀመርያ ጊዜ ዝቅተኛ የእንግሊዝኛ ብቃት ላላቸው ተጠቃሚዎች አገልግሎት አስተባባሪዎችን መመደብ እና የቋንቋ ተደራሽነት ተጠሪዎችን ማዋቀር፤
  • የዴንቨር የፖሊስ መምርያ ሰራተኞችን በሙሉና አዲስ ምልምሎችን ዝቅተኛ የእንግሊዝኛ ብቃት ያላቸውን ግለሰቦች እንዴት መለየት፣መቅረብ እንደሚኖርባቸውና ከግለሰቦቹም ጋር የነበሯቸውንም ተግባቦቶች በጽሁፍ ስለመመዘገብ ማሰልጠን፣ እና
  • ዝቅተኛ የእንግሊዝኛ ችሎታ ያላቸውን የማህበረሰብ አባላትን  ፍላጎት የሚወክሉ ባለድርሻ አካላትን የሚያካትት የቋንቋ ተደራሽነት ኮሚቴ ማቋቋም።

ስለ ዜጎች መብቶች መምሪያ ተጨማሪ መረጃ በ www.justice.gov/crt ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።
ውሱን የእንግሊዝኛ ብቃት እና ይህን መብት የሚመለከት የሕግ አንቀጽ VI መረጃ በ www.lep.gov ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል። በተጨማሪም የህብረተሰቡ አባላት ተፈጽሟል ብለው የሚያምኑበትን የዜጎች መብት ጥሰት
https://civilrights.justice.gov/report/ ድረ-ገጽ ላይ  ማመልከት ይችላሉ።


English

Amharic: አማርኛ

Arabic: العربية

Burmese: မြန်မာဘာသာ

Chinese, Simplified: 简体字

Chinese, Traditional: 簡體字

Farsi: فارسی

French: Français

Karen: ကညီ

Nepali:  नेपाली

Rohingya: Ruáingga  

Russian: Pусский

Somali: Soomaaliga

Spanish: Español

Vietnamese: Tiếng Việt

Updated May 27, 2023

Civil Rights
Press Release Number: 22-1385